ኢዮብ 26:1-14
26 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንከው!+
3 ጥበብ ለሌለው እንዴት ያለ ታላቅ ምክር ሰጠኸው!+
የጥበብህን* ብዛት* ምንኛ ገለጥክ!
4 ለማን ለመናገር እየሞከርክ ነው?እንዲህ ያለ ነገር እንድትናገር የገፋፋህስ ማን ነው?*
5 በሞት የተረቱት ይንቀጠቀጣሉ፤ከውኃዎችና በውስጣቸው ከሚኖሩት እንኳ በታች ናቸው።
6 መቃብር* በአምላክ* ፊት የተራቆተ ነው፤+የጥፋትም ስፍራ* አይሸፈንም።
7 የሰሜኑን ሰማይ* በባዶ ስፍራ* ላይ ዘርግቷል፤+ምድርንም ያለምንም ነገር አንጠልጥሏል፤
8 ውኃዎችን በደመናቱ ውስጥ ይጠቀልላል፤+ከክብደታቸውም የተነሳ ደመናቱ አይቀደዱም፤
9 ደመናውን በላዩ ላይ በመዘርጋት፣ዙፋኑን ይጋርዳል።+
10 በውኃዎቹ ገጽ ላይ አድማሱን* ያበጃል፤+በብርሃንና በጨለማ መካከል ወሰን ያደርጋል።
11 የሰማይ ዓምዶች ተናጉ፤ከተግሣጹም የተነሳ ደነገጡ።
12 ባሕሩን በኃይሉ ያናውጣል፤+በማስተዋሉም ግዙፉን የባሕር ፍጥረት* ይቆራርጣል።+
13 በእስትንፋሱ* ሰማያትን ያጠራል፤እጁ የማይጨበጠውን* እባብ ትወጋለች።
14 እነሆ፣ እነዚህ የመንገዱ ዳር ዳር ናቸው፤+ስለ እሱ የሰማነው የሹክሹክታ ያህል ብቻ ነው!
ታዲያ ኃይለኛ የሆነውን ነጎድጓዱን ማን ሊያስተውል ይችላል?”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ማስተዋል የታከለበት ጥበብህን።”
^ ወይም “ጥበብህን ሳትቆጥብ።”
^ ቃል በቃል “የማንስ እስትንፋስ (መንፈስ) ከአንተ ዘንድ ወጣ?”
^ ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ቃል በቃል “በእሱ።”
^ ወይም “አባዶንም።”
^ ቃል በቃል “በባዶ።”
^ ቃል በቃል “ሰሜኑን።”
^ ቃል በቃል “ክበብን።”
^ ቃል በቃል “ረዓብን።”
^ ወይም “በነፋሱ።”
^ ወይም “በፍጥነት የሚሳበውን።”