በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሁለተኛ ነገሥት መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ኤልያስ፣ አካዝያስ እንደሚሞት ትንቢት ተናገረ (1-18)

  • 2

    • ኤልያስ በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ (1-18)

      • ኤልሳዕ የኤልያስን የነቢይነት ልብስ ለበሰ (13, 14)

    • ኤልሳዕ የኢያሪኮን ውኃ ፈወሰ (19-22)

    • ድቦች ከቤቴል የወጡትን ልጆች ቦጫጨቁ (23-25)

  • 3

    • ኢዮራም በእስራኤል ላይ ነገሠ (1-3)

    • ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዓመፀ (4-25)

    • ሞዓብ ተሸነፈ (26, 27)

  • 4

    • ኤልሳዕ የመበለቷ ዘይት ከማሰሮው እንዳያልቅ አደረገ (1-7)

    • አንዲት ሹነማዊት ኤልሳዕን አስተናገደችው (8-16)

    • ሴትየዋ ልጅ በመውለድ ተባረከች፤ ልጇ ሞተ (17-31)

    • ኤልሳዕ ልጇን ከሞት አስነሳላት (32-37)

    • “ድስቱ ውስጥ ገዳይ መርዝ አለ” (38-41)

    • ኤልሳዕ በጥቂት ዳቦ ብዙ ሰው መገበ (42-44)

  • 5

    • ኤልሳዕ ንዕማንን ከሥጋ ደዌ ፈወሰው (1-19)

    • ስግብግብ የሆነው ግያዝ በሥጋ ደዌ ተመታ (20-27)

  • 6

    • ኤልሳዕ የመጥረቢያው አናት እንዲንሳፈፍ አደረገ (1-7)

    • ኤልሳዕና የሶርያ ሠራዊት (8-23)

      • የኤልሳዕ አገልጋይ ዓይኖች ተከፈቱ (16, 17)

      • ኤልሳዕ የሶርያውያኑን አእምሮ አሳወረ (18, 19)

    • በተከበበችው ሰማርያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ (24-33)

  • 7

    • ኤልሳዕ የረሃቡ ጊዜ እንደሚያበቃ ትንቢት ተናገረ (1, 2)

    • ሶርያውያን ጥለውት በሸሹት ጦር ሰፈር ብዙ ምግብ ተገኘ (3-15)

    • ኤልሳዕ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ (16-20)

  • 8

    • ሹነማዊቷ ሴት መሬቷ ተመለሰላት (1-6)

    • ኤልሳዕ፣ ቤንሃዳድና ሃዛኤል (7-15)

    • ኢዮራም በይሁዳ ላይ ነገሠ (16-24)

    • አካዝያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (25-29)

  • 9

    • ኢዩ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ተቀባ (1-13)

    • ኢዩ ኢዮራምንና አካዝያስን ገደላቸው (14-29)

    • ኤልዛቤል ተገደለች፤ ሥጋዋን ውሾች በሉት (30-37)

  • 10

    • ኢዩ የአክዓብን ቤት አጠፋ (1-17)

      • ኢዮናዳብ ከኢዩ ጎን ቆመ (15-17)

    • ኢዩ የባአል አምላኪዎችን ገደለ (18-27)

    • የኢዩ የግዛት ዘመን (28-36)

  • 11

    • ጎቶልያ በጉልበት ዙፋኑን ያዘች (1-3)

    • ኢዮዓስ በድብቅ እንዲነግሥ ተደረገ (4-12)

    • ጎቶልያ ተገደለች (13-16)

    • ዮዳሄ የወሰደው የተሃድሶ እርምጃ (17-21)

  • 12

    • ኢዮዓስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-3)

    • ኢዮዓስ ቤተ መቅደሱን ጠገነ (4-16)

    • የሶርያውያን ወረራ (17, 18)

    • ኢዮዓስ ተገደለ (19-21)

  • 13

    • ኢዮዓካዝ በእስራኤል ላይ ነገሠ (1-9)

    • ኢዮዓስ በእስራኤል ላይ ነገሠ (10-13)

    • ኤልሳዕ የኢዮዓስን ቅንዓት ፈተነ (14-19)

    • ኤልሳዕ ሞተ፤ የኤልሳዕን አፅም የነካው ሰው ከሞት ተነሳ (20, 21)

    • ኤልሳዕ የተናገረው የመጨረሻው ትንቢት ፍጻሜውን አገኘ (22-25)

  • 14

    • አሜስያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-6)

    • ከኤዶምና ከእስራኤል ጋር የተደረገ ውጊያ (7-14)

    • የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ሞተ (15, 16)

    • አሜስያስ ሞተ (17-22)

    • ዳግማዊ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ (23-29)

  • 15

    • አዛርያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-7)

    • መጨረሻ ላይ የነገሡት የእስራኤል ነገሥታት፦ ዘካርያስ (8-12)፣ ሻሉም (13-16)፣ መናሄም (17-22)፣ ፈቃህያህ (23-26)፣ ፋቁሄ (27-31)

    • ኢዮዓታም በይሁዳ ላይ ነገሠ (32-38)

  • 16

    • አካዝ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-6)

    • አካዝ ለአሦር ንጉሥ ጉቦ ሰጠ (7-9)

    • አካዝ የአረማውያንን መሠዊያ ንድፍ ወሰደ (10-18)

    • አካዝ ሞተ (19, 20)

  • 17

    • ሆሺአ በእስራኤል ላይ ነገሠ (1-4)

    • የእስራኤል ውድቀት (5, 6)

    • እስራኤላውያን ለግዞት ተዳረጉ (7-23)

    • በሰማርያ ከተሞች የባዕድ አገር ሰዎች እንዲሰፍሩ ተደረገ (24-26)

    • የሳምራውያን ቅይጥ አምልኮ (27-41)

  • 18

    • ሕዝቅያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-8)

    • የእስራኤል አወዳደቅ (9-12)

    • ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ (13-18)

    • ራብሻቁ ይሖዋን ተገዳደረ (19-37)

  • 19

    • ሕዝቅያስ፣ ይሖዋ እንዲረዳው ጠየቀ (1-7)

    • ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ዛተ (8-13)

    • ሕዝቅያስ ያቀረበው ጸሎት (14-19)

    • ኢሳይያስ አምላክ የሰጠውን መልስ ነገረው (20-34)

    • አንድ መልአክ 185,000 አሦራውያንን ገደለ (35-37)

  • 20

    • ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ዳነ (1-11)

    • ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች (12-19)

    • ሕዝቅያስ ሞተ (20, 21)

  • 21

    • ምናሴ በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ ብዙ ደምም አፈሰሰ (1-18)

      • ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ተነገረ (12-15)

    • አምዖን በይሁዳ ላይ ነገሠ (19-26)

  • 22

    • ኢዮስያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1, 2)

    • ቤተ መቅደሱ እንዲጠገን መመሪያ ሰጠ (3-7)

    • የሕጉ መጽሐፍ ተገኘ (8-13)

    • ሕልዳና ጥፋት እንደሚመጣ ትንቢት ተናገረች (14-20)

  • 23

    • ኢዮስያስ ያካሄደው ተሃድሶ (1-20)

    • የፋሲካ በዓል ተከበረ (21-23)

    • ኢዮስያስ የወሰደው ተጨማሪ እርምጃ (24-27)

    • ኢዮስያስ ሞተ (28-30)

    • ኢዮዓካዝ በይሁዳ ላይ ነገሠ (31-33)

    • ኢዮዓቄም በይሁዳ ላይ ነገሠ (34-37)

  • 24

    • ኢዮዓቄም ዓመፀ፤ በኋላም ሞተ (1-7)

    • ዮአኪን በይሁዳ ላይ ነገሠ (8, 9)

    • ለመጀመሪያ ጊዜ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰዱ (10-17)

    • ሴዴቅያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ እንዲሁም ዓመፀ (18-20)

  • 25

    • ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ከበበ (1-7)

    • ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን አጠፋ፤ ሕዝቡ ለሁለተኛ ጊዜ በግዞት ተወሰደ (8-21)

    • ናቡከደነጾር ጎዶልያስን አለቃ አድርጎ ሾመው (22-24)

    • ጎዶልያስ ተገደለ፤ ሕዝቡ ወደ ግብፅ ሸሸ (25, 26)

    • ዮአኪን ከእስር ተፈታ (27-30)