በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥላቻን ድል ማድረግ እንችላለን!

ጥላቻን ድል ማድረግ እንችላለን!

የጥላቻ ሰለባ ሆነህ ታውቃለህ?

አንተ በግልህ የጥላቻ ሰለባ ሆነህ ባታውቅም እንኳ በሌሎች ላይ ሲደርስ አይተህ መሆን አለበት። የዜና ማሰራጫዎች ሰዎች በዘራቸው፣ በፆታቸው ወይም በትውልድ አገራቸው ምክንያት ስለሚደርስባቸው ጥላቻ በሚገልጹ ዘገባዎች የተሞሉ ናቸው። በዚህም የተነሳ በርካታ መንግሥታት፣ በጥላቻ ምክንያት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የተለያዩ ሕጎችን እያወጡ ነው።

ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል። የጥላቻ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የበቀል እርምጃ ይወስዳሉ፤ ይህም ቀጣይ የሆነ የጥላቻ ሰንሰለት እንዲኖር ያደርጋል።

ምናልባት መድልዎ፣ ፌዝ፣ ስድብ ወይም ዛቻ ደርሶብህ ያውቅ ይሆናል። ሆኖም ጥላቻ ብዙውን ጊዜ በዚህ ብቻ አያበቃም። ጥላቻ እንደ ጉልበተኝነት፣ ንብረት ማውደም፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የነፍስ ግድያ አልፎ ተርፎም የዘር ጭፍጨፋ ወዳሉ የጭካኔ ድርጊቶች ይመራል።

ይህ መጽሔት ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፤ እንዲሁም ጥላቻን ድል ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል፦

  • ጥላቻ ይህን ያህል የተስፋፋው ለምንድን ነው?

  • የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ጥላቻ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበት ዘመን ይመጣ ይሆን?