መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 2 2019 | ሕይወት መራራ ሆኖብሃል?
በሕይወትህ ውስጥ ያጋጠመህ አሳዛኝ ሁኔታ ‘በሕይወት መኖር ምን ዋጋ አለው?’ ብለህ እንድታስብ አድርጎሃል?
ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ
ምንም ዓይነት ከባድ ሁኔታ ቢያጋጥምህ በሕይወት መኖርህ ዋጋ አለው።
የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ካጋጠመህ የተፈጥሮ አደጋ እንድታገግም የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።
የምትወደው ሰው ሲሞት
የምትወደውን ሰው በሞት ማጣትህ ያስከተለብህን ሐዘን ለመቋቋም የሚረዱህን አምስት ጠቃሚ ምክሮች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
የትዳር ጓደኛ ክህደት ሲፈጽም
የትዳር ጓደኛቸው ክህደት የፈጸመባቸው በርካታ ባለትዳሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽናኛ ማግኘት ችለዋል።
ከከባድ ሕመም ጋር ስትታገል
ከከባድ ሕመም ጋር የሚታገሉ አንዳንድ ሰዎች ሁኔታውን መቋቋም የቻሉት እንዴት እንደሆነ አንብብ።
ሞተህ መገላገል ስትመኝ
በከባድ ጭንቀት ከመዋጥህ የተነሳ ሕይወትህን ለማጥፋት ያሰብክበት ጊዜ አለ? በዚህ ወቅት እርዳታ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?
በሕይወት መኖር ዋጋ አለው!
ያለህበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሰዎች ባይረዱልህ እንኳ አምላክ እንደሚያስብልህና ከጎንህ ሆኖ እንደሚደግፍህ እርግጠኛ ሁን።
“እሱ ስለ እናንተ ያስባል”
እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሊያጽናኑህና ሊያበረታቱህ ይችላሉ።