መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 3 2018 | አምላክ ለአንተ ያስብልሃል?
አምላክ ለአንተ ያስብልሃል?
አደጋ ሲከሰት ወይም ሰዎች ሲሠቃዩና ሲሞቱ ስንመለከት ‘አምላክ ይህን ሁኔታ ያያል? ከነጭራሹስ ግድ ይሰጠዋል?’ ብለን እናስብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ፤ የይሖዋ ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው።”—1 ጴጥሮስ 3:12
ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ እርዳታ የሚያደርግልን እንዴት እንደሆነና ማንኛውንም ዓይነት መከራ ለማስወገድ በቅርቡ ምን እርምጃ እንደሚወስድ ይገልጻል።
“አምላክ የት ነበር?”
የደረሰብህ አሳዛኝ ሁኔታ አምላክ በግለሰብ ደረጃ ለአንተ የሚያስብልህ መሆኑን እንድትጠራጠር አድርጎህ ይሆን?
አምላክ ትኩረት ይሰጥሃል?
አምላክ ለደህንነታችን ከልብ እንደሚያስብ የሚሳይ ምን ማስረጃ አለ?
አምላክ ስሜትህን ይረዳልሃል?
አምላክ ስለ እኛም ሆነ ስለ ጄኔቲካዊ አወቃቀራችን ያለው ከሁሉ የላቀ እውቀት ስሜታችንን በሚገባ እንደሚረዳልን እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።
አምላክ ሥቃያችን ይሰማዋል?
መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ትኩረት እንደሚሰጠን፣ ስሜታችንን እንደሚረዳልንና እንደሚራራልን ያረጋግጥልናል።
መከራ የአምላክ ቅጣት ነው?
አምላክ ሰዎችን ለሠሩት ኃጢአት ለመቅጣት ሲል በበሽታ እንዲሠቃዩ ወይም ሌሎች ችግሮች እንዲደርሱባቸው ያደርጋል?
ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ዘር ላይ ለሚደርሰው መከራ ሦስት ዋና ዋና መንስኤዎችን ይጠቅሳል።
በቅርቡ አምላክ መከራን ሁሉ ያስወግዳል
በቅርቡ አምላክ መከራንና የፍትሕ መጓደልን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እርምጃ እንደሚወስድ እንዴት ማወቅ እንችላለን?
አምላክ እንደሚያስብልህ ማወቅህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ወደፊት አስደሳች ሕይወት እንደሚሰጠን በገባው ቃል ላይ እምነት ለመጣል ይረዳናል።
አምላክ በአንተ ላይ ስለሚደርሰው መከራ ምን ይሰማዋል?
እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አምላክ ስለሚደርስብህ መከራ ምን እንደሚሰማው ለማወቅ ይረዱሃል።