ንቁ! ቁጥር 1 2022 | ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ—ኑሮን በዘዴ
የዓለም ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ነው፤ የተፈጥሮ አደጋዎችና ሰው ሠራሽ ችግሮች አሁን አሁን የእያንዳንዳችንን ቤት እያንኳኩ ነው። ታዲያ እነዚህን ችግሮች ለመቋቋም ምን ይረዳሃል? በአንተም ሆነ በቤተሰብህ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስስ ምን ማድረግ ትችላለህ? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ—ኑሮን በዘዴ
አንድ አሳዛኝ ሁኔታ ሲከሰት፣ ራስህንም ሆነ ቤተሰብህን ለመጠበቅ ቶሎ እርምጃ መውሰድ አለብህ።
1 | ጤንነትህ
ጥሩ ጤንነት አስጨናቂ ሁኔታዎችን ለመቋቋም የተሻለ አቅም ይሰጥሃል።
2 | መተዳደሪያህ
ገንዘብህን በአግባቡ የምትይዝ ከሆነ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት የተሻለ ዝግጁነት ይኖርሃል።
3 | ከሌሎች ጋር ያለህ ግንኙነት
ከትዳር አጋርህ፣ ከጓደኞችህና ከልጆችህ ጋር ያለህን ግንኙነት ለመጠበቅ የሚረዱህን ጠቃሚ ምክሮች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
4 | ተስፋህ
መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመወጣት ይረዳናል፤ ስለ ወደፊቱ ጊዜም ብሩህ ተስፋ ይሰጠናል።
በዚህ የንቁ! እትም ላይ
የሰው ዘር ከገጠመው ቀውስ ራስህንም ሆነ ቤተሰብህን ለመጠበቅ የሚረዱ ርዕሶችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።