በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐዘን ላይ ለሚገኙ ሰዎች የሚሆን እርዳታ

ሐዘን ላይ ለሚገኙ ሰዎች የሚሆን እርዳታ

ሐዘን ላይ ለሚገኙ ሰዎች የሚሆን እርዳታ

የ12 ዓመት ልጅ እያለች አባቷን በሞት ያጣች አንዲት ሴት ለበርካታ ዓመታት በመንፈስ ጭንቀት ትሠቃይ ነበር። ወደ ካናዳ ቅርንጫፍ ቢሮ በላከችው ደብዳቤ ላይ እንደሚከተለው ብላ ነበር:-

“የምትወዱት ሰው ሲሞት የሚለውን ብሮሹር አግኝቼ እስካነበብኩበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ማጽናኛ ማግኘት አልቻልኩም ነበር። ብሮሹሩ ሐዘኔን መቋቋም እንድችል ረድቶኛል። አሁንም ድረስ አባቴን በሞት እንዳጣሁት ሳስብ አለቅሳለሁ። ሆኖም ብሮሹሩን በማንበቤ፣ ባነበብኩት ነገር ላይ በማሰላሰሌ፣ በመጸለዬ እንዲሁም ብሮሹሩንም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማነብበት ጊዜ ሲቃ ሲተናነቀኝ ከማልቀስ ወደ ኋላ ባለማለቴ ቀድሞ ይሰማኝ የነበረውን መጥፎ ስሜት መቋቋም የቻልኩ ሲሆን አሁን አምላክ በገባቸው ተስፋዎች መጽናናት ችያለሁ።

“በብሮሹሩ ውስጥ ያሉት ሐሳቦችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተሰበረውን ልቤን ለመጠገን በጣም ስለረዱኝ በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው። አሁን እንዳገገምኩ ይሰማኛል። ብሮሹሩ ከሁሉ የተሻለ እርዳታ የያዘ በመሆኑ በሐዘን ውስጥ የሚገኙ ሰዎች እንዲያነቡት አበረታታቸዋለሁ።”

እርስዎም የሚወዱትን ሰው በሞት አጥተዋል? ሐዘኑ ከልብዎ አልወጣ ብሎዎታል? ሐዘንዎን ለመቋቋም የሚረዳዎ ነገር ለማግኘት ይፈልጋሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ሙታን ስላላቸው ተስፋ ምን ይናገራል? እርስዎ ራስዎ አሊያም አንድ ሌላ የሚያውቁት ሰው፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት የሚለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ ማጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ይህን ብሮሹር ማግኘት የሚፈለጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።