በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኒካራጓ ሐይቅ ጉልህ ገጽታ ሁለቱን የእሳተ ገሞራ ተራሮች የሚያገናኝ ለም መሬት ያለው የኦሜቴፔ ደሴት ነው

አገሮችና ሕዝቦች

ኒካራጓን እንጎብኝ

ኒካራጓን እንጎብኝ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ኒካራጓን የሐይቆችና የእሳተ ገሞራዎች አገር ብለው ይጠሯታል። በመካከለኛው አሜሪካ ከሚገኙት ሐይቆች ሁሉ ትልቅ የሆነው የኒካራጓ ሐይቅ የሚገኘው በዚህች አገር ነው። የአገሬው ተወላጅ የሆኑ ጎሳዎች ኮሲቦካ በማለት የሚጠሩት ሲሆን ትርጉሙም “ጣፋጭ ባሕር” ማለት ነው። ይህ ሐይቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደሴቶች ያሉት ሲሆን እንደ ሻርክ፣ ሶርድ ፊሽና ታርፐን የመሳሰሉ ውቅያኖስ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳትን የያዘ ብቸኛው ጨዋማ ያልሆነ ሐይቅ ነው።

ሳኩዋንጆቼ (ፍራንጂፓኒ) የሚባለው የኒካራጓ ብሔራዊ አበባ

በመካከለኛው አሜሪካ በጣም ተገልለው ከሚገኙት አካባቢዎች አንዱ የሆነው የሞስኪቶ የባሕር ጠረፍም የሚገኘው በኒካራጓ ነው። ሥልሳ አምስት ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ይህ ቦታ አብዛኛውን ምሥራቃዊ ዳርቻ ይዞ ጎረቤት አገር እስከሆነችው እስከ ሆንዱራስ ይዘልቃል። የሚስኪቶ ጎሳ (የሞስኪቶ ሌላኛው አጠራር ነው) የኒካራጓ ተወላጅ ከሆኑ በርከት ያሉ ጎሳዎች መካከል አንዱ ሲሆን አውሮፓውያን በ16ኛው መቶ ዘመን ወደዚያ ከመምጣታቸው በፊት አንስቶ ይኖር የነበረ ጎሳ ነው።

ሚስኪቶዎች ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስርና ለየት ያለ ባሕል ያላቸው ሕዝቦች ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ በሚስኪቶ ቋንቋ እንደ “አቶ” ወይም “ወይዘሮ” ያሉ የማዕረግ ስሞች አይገኙም። በገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች ዘመዶቻቸው ባይሆኑም እንኳ ታላላቆቻቸውን “አጎቴ” ወይም “አክስቴ” ብለው ይጠሯቸዋል። በሚስኪቶ ጥንታዊ ባሕል መሠረት ሴቶች ከቅርብ ጓደኞቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ሰላምታ የሚለዋወጡት ጉንጭና ጉንጫቸውን በማነካካት ነው። ከዚያም ቀድማ ሰላምታ የሰጠችው ሴት በአፍንጫዋ አየር ትስባለች።

የአገሪቱ ተወላጆች

በማያንኛ እና በሚስኪቶ ቋንቋ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ ጽሑፎች