በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የ2010 የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም

የ2010 የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም

የ2010 የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም

መስከረም 21-23, 2003/ጥቅምት 1-3, 2010

በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ፣ አማርኛ

መስከረም 28-30, 2003/ጥቅምት 8-10, 2010

በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ፣ አማርኛ እና የምልክት ቋንቋ

አምቦ፣ ኦሮምኛ *

ይርጋለም፣ ሲዳምኛ

ናዝሬት፣ አማርኛ

ጥቅምት 5-7, 2003/ጥቅምት 15-17, 2010

በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ፣ አማርኛ

አለታወንዶ፣ አማርኛ

ደሴ፣ አማርኛ

ነቀምቴ፣ አማርኛ *

ሻሸመኔ፣ አማርኛ

ጥቅምት 12-14, 2003/ጥቅምት 22-24, 2010

በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ፣ አማርኛ

አዲስ አበባ፣ እንግሊዝኛ *

ድሬዳዋ፣ አማርኛ

ሶዶ፣ አማርኛ

ጊምቢ፣ ኦሮምኛ *

ጥቅምት 19-21, 2003/ጥቅምት 29-31, 2010

በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ፣ አማርኛ

መቀሌ፣ ትግርኛ *

ሶዶ፣ ወላይትኛ

ጅማ፣ አማርኛ

ባሕር ዳር፣ አማርኛ *

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.6 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

^ አን.13 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

^ አን.17 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

^ አን.20 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

^ አን.23 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

^ አን.26 ለሁለት ቀናት ማለትም ቅዳሜና እሁድ ብቻ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቦታዎች።

ከአፍሪካ የተገኙ ተሞክሮዎች

አገሮች 57 የሕዝብ ብዛት 878,000,158 አስፋፊዎች 1,171,674 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች 2,382,709

ቤኒን ክሎድና ባለቤቱ ማሪክሌር ለ27 ዓመታት በሚስዮናዊነት በቅንዓት አገልግለዋል። በየካቲት ወር ማሪክሌር ወድቃ እግሯ ተሰበረ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ደግሞ ባለቤቷ ክሎድ በሚስዮናውያን ቤት ውስጥ እየሠራ እያለ ወድቆ እግሩ ተሰበረ። ማሪክሌር ቀኝ እግሯ ክሎድ ደግሞ ግራ እግሩ በጀሶ ታሸገ። ክሎድ “ሁልጊዜ ነገሮችን አንድ ላይ ማድረግ ያስደስተናል!” በማለት በቀልድ ተናግሯል።

ክሎድ የተደረገለት ጀሶ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስ የሚከለክለው አልነበረም፤ ማሪክሌር ግን ለሳምንታት ከቤት ሳትወጣ ቆይታለች። ከነበሯት 12 ጥናቶች መካከል 4ቱን በሚስዮናውያን ቤት ማስጠናት ብትችልም በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች መካፈል አልቻለችም። በመሆኑም በቤታቸው ፊት ለፊት በመቀመጥ ጠረጴዛ ላይ በርከት ያሉ ጽሑፎችን ዘርግታ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎችን ለማነጋገር ወሰነች። በመጋቢት ወር በዚህ መንገድ 83 ሰዓታት አሳልፋለች። ይሖዋ ያደረገችውን ጥረት ባርኮላት ይሆን? በዚያ ወር 14 መጻሕፍት፣ 452 ብሮሹሮች፣ 290 መጽሔቶችና ከ500 በላይ ትራክቶችን አበርክታለች።

ኢትዮጵያ ከከተማ ርቆ በሚገኝ ገጠራማ አካባቢ የሚኖረው አረጋ የቤቱን ግድግዳ በወረቀት ለመለጠፍ አሰበ። በዚያ አገር አንዳንድ ሰዎች ለዚህ ዓላማ ጋዜጣ የሚጠቀሙ ቢሆኑም እሱ ግን የሚያምር ወረቀት ማግኘት ፈለገ። ገበያ ውስጥ አንድ ሰው በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክት ተመለከተ። አረጋ አንድ ቅጂ ወስዶ ምንም ሳያነበው ከገነጣጠለው በኋላ ገጾቹን በቤቱ ግድግዳ ላይ ለጠፋቸው። ከሁለት ዓመታት በኋላ ግድግዳው ላይ በለጠፈው ወረቀት ላይ “ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነበር” የሚል ዓረፍተ ነገር አነበበ። ይህ ሐሳብ እሱ ከተማረው የሥላሴ ትምህርት የተለየ ሆነበት። አረጋ የማወቅ ፍላጎት ስላደረበት አምላክ ልጅ አለው ብለው የሚያስተምሩ ሰዎችን ለማግኘት ዘጠኝ ሰዓት በእግሩ ተጉዞ በጣም ቅርብ ወደሚባለው ከተማ ሄደ። የመጀመሪያ ሙከራው ስኬታማ ስላልነበረ ተስፋ ቆርጦ ወደቤቱ ተመለሰ። ከጊዜ በኋላ እንደገና ሞከረ፤ በዚህ ጊዜ ግን ሰዎች ብሮሹሩን የሰጠው ወንድም የሚኖርበትን ቤት ጠቆሙት። አረጋ በዚህ ጊዜም ትዕግሥት የሚፈታተን ሁኔታ አጋጠመው፤ ወንድም ወደ ቤቱ እስኪመጣ ድረስ ለሰዓታት መጠበቅ ነበረበት። ወንድም ከመጣ በኋላ ውይይት አድርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረ። በቀጣዮቹ ወራት አረጋ በተደጋጋሚ ወደ ከተማ እየሄደ የአምላክን እውቀት መቅሰሙን ቀጠለ። የተማረውን ነገር ለመንደሩ ሰዎች ሲነግራቸው ከባድ ተቃውሞ ያጋጠመው ከመሆኑም በላይ ብዙ ሰዎች አገለሉት። እሱ ግን በዚህ ተስፋ አልቆረጠም፤ በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ሌሎች ሰዎች ማግኘት ችሏል። የእነዚህ ሰዎች ቁጥር 13 ሲደርስ ሁለት ልዩ አቅኚዎች ተመደቡ። እነዚህ ልዩ አቅኚዎች ብዙም ሳይቆይ ከ40 የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን አገኙ፤ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ይገኙ ነበር። በአሁኑ ጊዜ በአካባቢው ስምንት አስፋፊዎች ይገኛሉ። አሁን ወንድማችን የሆነው አረጋ በግድግዳው ላይ የለጠፋቸው ሥዕሎች ቤቱን ከማሳመር የበለጠ ጥቅም ሰጥተውታል።

ጋና በመላው አፍሪካ በፍጥነት እየተሰራጨ በሚገኘው የሞባይል ስልክ ምክንያት “የመገናኛ አብዮት” እየተካሄደ እንዳለ ይነገራል። በርካታ ድርጅቶች ደንበኛ ለመሳብ ሌሊት ለተወሰኑ ሰዓታት ነፃ ጥሪ ማድረግ የሚቻልበትን ዝግጅት አድርገዋል። ግሬስ የተባለች አንዲት እህት በዚህ ዝግጅት ተጠቅማለች። ሞኒካ የምትባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቷ በሌሎች ጉዳዮች ጊዜዋ በጣም ስለተጣበበ እሷን ማስጠናት አስቸጋሪ ሆኖባት ነበር። ግሬስ ጥናቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ያላደረገችው ነገር አልነበረም፤ ሌላው ቀርቶ ከማለዳው 11:00 ሰዓት ሞኒካ ቤት እንዲያጠኑ ዝግጅት አድርጋ ነበር። ይሁንና የሞኒካ ፕሮግራም ስለተለወጠ በዚህም ሰዓት ማጥናት አልተቻለም። በመሆኑም ግሬስ ሌሊት ላይ ነፃ ጥሪ ማድረግ የሚቻልበትን ሰዓት ለመጠቀም አሰበች። ሞኒካ በሐሳቡ የተስማማች ሲሆን ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ላይ በስልክ ለማጥናት ዝግጅት አደረጉ። የሚያሳዝነው ግን በዚህ ሰዓት ብዙ ተጠቃሚዎች በመኖራቸው ምክንያት ኔትወርክ ስለሚጨናነቅ መስመር ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ሆነባቸው። በዚህም ምክንያት ቀደም ብለው ለመነሳትና 9:00 ሰዓት ላይ ለማጥናት ዝግጅት አደረጉ፤ እርግጥ ሁለቱም ሥራ ውለው የሚገቡ እናቶች በመሆናቸው እንዲህ ማድረጉ ቀላል ሆኖ አላገኙትም። ግሬስ እንዲህ ትላለች፦ “ጥናቴ ያላት ፍላጎት እንዳይቀዘቅዝ ማድረግ እንድችል ይሖዋ የሚያስፈልገኝን ብርታትና ፍላጎት እንዲሰጠኝ ለመንኩት። በምፈልገው ሰዓት ለመንቃት ስልኬን ሞላሁና በዚያ ሰዓት ለመነሳት ቁርጥ ውሳኔ አደረግኩ። በጣም የሚደክመኝ የነበረ ቢሆንም ይህ ተስፋ እንዲያስቆርጠኝ አልፈለግኩም።” ሞኒካ በ2008 በተደረገው “በአምላክ መንፈስ መመራት” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ በመጠመቋ ግሬስ የከፈለችው መሥዋዕትነት ከንቱ ስላልሆነ በጣም ተደስታ ነበር። ግሬስ በቅርቡ በሌሊት ነፃ ጥሪ የሚደረግበትን ሰዓት ተጠቅማ በአሁኑ ጊዜ ስብሰባ ላይ መገኘት የጀመረችን ሌላ ሴት ማስጠናት ጀምራለች።

ሞዛምቢክ በነሐሴ 2008 አንድ መኪና እያለፈ እያለ አንድ ጃኬት ከመኪናው ውስጥ ወደቀ፤ ጃኬቱ የወደቀው የይሖዋ ምሥክር በሆኑ አንዲት ድሃ መበለት ጎጆ አጠገብ ነበር። እኚህ እህት ጃኬቱን አንስተው ሲመለከቱ ኪሱ ውስጥ አንዳንድ ሰነዶች፣ በጣም ውድ ጌጣጌጦችን የያዙ ሦስት ትናንሽ ቦርሳዎች እንዲሁም ወደ አንድ ሺህ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አገኙ። እህት በዚያ መንደር የሚኖር አንድ ሰው ለምነው በሰነዶቹ ላይ ባሉት ቁጥሮች ተጠቅሞ ስለጠፋው ንብረት እንዲነግርላቸው አደረጉ። ያን ዕለት ምሽት አራት ሰዎች በመኪና ወደ መንደሩ መጡ። እህታችን የመንደሩ ባለሥልጣናት በተገኙበት ጃኬቱን አንድ ንብረት ሳይጎድል ለባለቤቱ አስረከቡ። ሰውየው ይህን ሲመለከት እያለቀሰ ንብረቱ በይሖዋ ምሥክሮች እጅ ውስጥ ባይወድቅ ኖሮ ንብረቱን የማግኘት አጋጣሚው በጣም ጠባብ እንደሆነ ተናገረ። ታማኟ እህታችን ድሃ ቢሆኑም በአካባቢው ለአምላካቸው ለይሖዋ ስም ትልቅ ውዳሴ ያመጣ ምሥክርነት መስጠት ችለዋል።