በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጋቢት 3-9

ምሳሌ 3

ከመጋቢት 3-9

መዝሙር 8 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. በይሖዋ እንደምትታመኑ አሳዩ

(10 ደቂቃ)

በራሳችሁ ሳይሆን በይሖዋ ታመኑ (ምሳሌ 3:5ijwbv ርዕስ 14 አን. 4-5)

የይሖዋን መመሪያ በመፈለግና በመከተል በእሱ እንደምትታመኑ አሳዩ (ምሳሌ 3:6ijwbv ርዕስ 14 አን. 6-7)

ከልክ በላይ በራሳችሁ አትተማመኑ (ምሳሌ 3:7be 76 አን. 4)

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በሁሉም የሕይወቴ ክፍሎች የይሖዋን መመሪያ እፈልጋለሁ?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 3:3—ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን በአንገታችን ዙሪያ ማሰርና በልባችን ጽላት ላይ መጻፍ የምንችለው እንዴት ነው? (w06 9/15 17 አን. 7)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ለተለመደ የተቃውሞ ሐሳብ ምላሽ ስጥ። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ስለ jw.org ንገረው፤ ከዚያም የአድራሻ ካርድ ስጠው። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) w11 3/15 14 አን. 7-10—ጭብጥ፦ በአገልግሎት ላይ ሰዎች ግድየለሽ ሲሆኑ በአምላክ ታመኑ። (th ጥናት 20)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 124

7. በይሖዋ ድርጅት እንደምትተማመኑ አሳዩ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በመንፈስ መሪነት በተጻፈው በአምላክ ቃል ውስጥ በሚገኘው መመሪያ መተማመን ብዙም ላይከብደን ይችላል። ይሁንና በይሖዋ ድርጅት ውስጥ አመራር ከሚሰጡት ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች በምናገኘው መመሪያ መተማመን ይከብደን ይሆናል፤ በተለይ መመሪያው ካልገባን ወይም ካላሳመነን ይበልጥ ሊከብደን ይችላል።

ሚልክያስ 2:7ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ይሖዋ ሕዝቦቹን ለመምራት ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች የሚጠቀም መሆኑ የማያስገርመን ለምንድን ነው?

ማቴዎስ 24:45ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ከይሖዋ ድርጅት በምናገኘው መመሪያ መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው?

ዕብራውያን 13:17ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ይሖዋ አመራር እንዲሰጡን የሚተማመንባቸው ወንድሞች የሚያደርጉትን ውሳኔ መደገፍ ያለብን ለምንድን ነው?

የ2021 የበላይ አካሉ ሪፖርት ቁጥር 9—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • በወረርሽኙ ወቅት ያገኘነው መመሪያ በይሖዋ ድርጅት ላይ ያላችሁን እምነት ያጠናከረላችሁ እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 57 እና ጸሎት