ሰኔ 12, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 25, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘አንድ ሆነን ይሖዋን ማገልገል’
ሐምሌ 24, 2024 በኦርዮል ከተማ የሚገኘው የሶቪየትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዲሚትሪ ኢግናቶቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ ወንድም ዲሚትሪ ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንዲሠራ ተፈርዶበታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ማረሚያ ቤት ውስጥ እየኖረ በከተማው ውስጥ በተመደበበት ቦታ እንዲሠራ ይደረጋል። የእስራት ጊዜውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ከደሞዙ 5 በመቶ የሚሆነውን መንግሥት ይወስደዋል።
አጭር መግለጫ
ዲሚትሪ እና ዳርያ ለተዉልን ምሳሌ አመስጋኞች ነን፤ የእነሱ ተሞክሮ እንደሚያረጋግጠው ‘በላይ ባሉት ነገሮች ላይ ካተኮርን’ በፈተና ውስጥም እንኳ መንፈሳዊ ሚዛናችንን መጠበቅ እንችላለን።—ቆላስይስ 3:2
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 9, 2020
ቤታቸው ተፈተሸ
ጥቅምት 28, 2021
የክስ ፋይል ተከፈተበት
መስከረም 13, 2023
ቤታቸው እንደገና ተፈተሸ
መጋቢት 4, 2024
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ