ለየዕለቱ የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለው ቡክሌት ለእያንዳንዱ ቀን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲሁም ለጥቅሱ የሚሆን ማብራሪያ ይዟል። ይህ ጽሑፍ እያንዳንዱን ቀን ጠቃሚ በሆኑና በሚያበረታቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ለመጀመር ያስችላል።
የዕለቱን ጥቅስም ሆነ ማብራሪያውን በቀኑ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ላይ ማንበብ ቢቻልም ብዙዎች ጠዋት ላይ የዕለቱን ጥቅስ ማንበብ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። እንዲህ ማድረጋቸው ባነበቡት ሐሳብ ላይ ቀኑን ሙሉ ለማሰላሰል አስችሏቸዋል። የምትኖረው ከቤተሰብህ ጋር ከሆነ በዕለቱ ጥቅስ ላይ ከቤተሰብህ ጋር መወያየትም ትችላለህ።
የዕለቱን ጥቅስ ከመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ላይ ማንበብ ትችላለህ፤ አሊያም ለዓመቱ የተዘጋጁትን ጥቅሶች በሙሉ በPDF ፋይል ማውረድ ትችላለህ (PDF ፋይሉ ከታተመው ጽሑፍ ጋር አንድ ዓይነት ነው)።